Psalms 106
World English Bible (en) → Amharic Bible (am)
- 1
ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።
- 2
የእግዚአብሔርን ኃይል ሥራ ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ያሰማል?
- 3
ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ምስጉኖች ናቸው።
- 4
አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበን፥ በመድኃኒትህም ጐብኘን፤
- 5
የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እንጓደድ ዘንድ።
- 6
ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአትን ሠራን፥ ዐመፅንም፥ በደልንም።
- 7
አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥ የምሕረትህንም ብዛት አላሰቡም፤ በኤርትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ።
- 8
ኃይሉን ግን ለማስታወቅ። ስለ ስሙ አዳናቸው።
- 9
የኤርትራንም ባሕር ገሠጸ እርሱም ደረቀ፤ እንደ ምድረ በዳ በጥልቅ መራቸው።
- 10
ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው።
- 11
ያሳደዱአቸውንም ውኃ ደፈናቸው፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም።
- 12
በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ።
- 13
ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልታገሡም።
- 14
በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
- 15
የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።
- 16
ሙሴንም እግዚአብሔር የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው።
- 17
ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፤
- 18
በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባልም ኅጥኣንን አቃጠላቸው።
- 19
በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
- 20
ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ።
- 21
- 22
እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።
- 23
የተወደደችውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥
- 24
በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
- 25
- 26
በብዔል ፌጎርም ተባበሩበት፥ የሙታንንም መሥዋዕት በሉ።
- 27
በሥራቸውም አስመረሩት፥ ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
- 28
ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፤
- 29
ያም እስከ ዘላለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።
- 30
- 31
እግዚአብሔርም እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፤
- 32
ከአሕዛብም ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።
- 33
ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ ወጥመድም ሆኑባቸው።
- 34
ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠው፤
- 35
የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸን ደም፥ ለከነዓን ጣዖቶች የሠውአቸውን ንጹሕ ደም አፈሰሱ፥ ምድርም በደም ረከሰች።
- 36
በሥራቸው ረከሱ፥ በማድረጋቸውም አመነዘሩ።
- 37
የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፥ ርስቱንም ተጸየፈ።
- 38
ወደ አሕዛብም እጅ አሳለፋቸው፥ የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።
- 39
ጠላቶቻቸውም ግፍ አደረጉባቸው፥ ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ።
- 40
ብዙ ጊዜ አዳናቸው፤ ነገር ግን በምክራቸው አስመረሩት፥ በኃጢአታቸውም ተዋረዱ።
- 41
እርሱ ግን ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ ጭንቃቸውን ተመለከተ፤
- 42
ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ምሕረቱም ብዛት ተጸጸተ።
- 43
በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።
- 44
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን።
- 45
ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል። ሃሌ ሉያ።