Psalms 105
World English Bible (en) → Amharic Bible (am)
- 1
እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ።
- 2
ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
- 3
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
- 4
እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
- 5
- 6
ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ።
- 7
እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።
- 8
ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥
- 9
ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤
- 10
ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና።
- 11
እንዲህም አለ። ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤
- 12
ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።
- 13
ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።
- 14
- 15
በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።
- 16
በፊታቸው ሰውን ላከ፤ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ።
- 17
እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥ እርሱም በብረት ውስጥ ገባ።
- 18
ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።
- 19
ንጉሥ ላከ ፈታውም፥ የአሕዛብም አለቃ አስፈታው።
- 20
የቤቱ ጌታ፥ የጥሪቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፥
- 21
አለቆቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
- 22
እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።
- 23
ሕዝቡንም እጅግ አበዛ፥ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው።
- 24
ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ በባሪያዎቹም ላይ ይተነኰሉ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ።
- 25
ባሪያውን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።
- 26
የተኣምራቱን ነገር በላያቸው ድንቁንም በካም አገር አደረገ።
- 27
ጨለማን ላከ ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።
- 28
ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።
- 29
ምድራቸው የንጉሦቻቸውም ቤቶች በጓጕንቸር ሞሉ።
- 30
ተናገረ፥ የውሻ ዝንብ ትንኝም በዳርቻቸው መጡ።
- 31
ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ እሳትም በምድራቸው ተቃጠለች።
- 32
ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የአገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
- 33
ተናገረ፥ አንበጣም ስፍር ቍጥር የሌለውም ኩብኩባ መጣ፥
- 34
የአገራቸውንም ለምለም ሁሉ በላ፥ የምድራቸውንም ፍሬ በላ።
- 35
የአገራቸውንም በኵር ሁሉ፥ የጕልበታቸውን መጀመሪያ ሁሉ መታ።
- 36
ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም።
- 37
ፈርተዋቸው ነበርና ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት።
- 38
ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት ያበራላቸው ዘንድ ዘረጋ።
- 39
ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
- 40
ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈሰሰ፤ ወንዞች በበረሃ ሄዱ፤
- 41
ለባሪያው ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስቦአልና።
- 42
ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ።
- 43
የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ የወገኖችንም ድካም ወረሱ፥
- 44
ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ