Numbers 33
World English Bible (en) → Amharic Bible (am)
- 1
የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን እጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ።
- 2
ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ፤ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ።
- 3
በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ።
- 4
በዚያም ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው።
- 5
የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተጕዘው በሱኮት ሰፈሩ።
- 6
ከሱኮትም ተጕዘው በምድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤታም ሰፈሩ።
- 7
ከኤታምም ተጕዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ።
- 8
ከፊሀሒሮትም ተጕዘው በባሕሩ ውስጥ ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ።
- 9
ከማራም ተጕዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም አሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ።
- 10
ከኤሊምም ተጕዘው በኤርትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ።
- 11
ከኤርትራም ባሕር ተጕዘው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ።
- 12
ከሲን ምድረ በዳም ተጕዘው በራፋቃ ሰፈሩ።
- 13
ከራፋቃም ተጕዘው በኤሉስ ሰፈሩ።
- 14
ከኤሉስም ተጕዘው በራፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም።
- 15
ከራፊዲምም ተጕዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።
- 16
ከሲናም ምድረ በዳ ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ።
- 17
ከምኞት መቃብርም ተጕዘው በሐጼሮት ሰፈሩ።
- 18
ከሐጼሮትም ተጕዘው በሪትማ ሰፈሩ።
- 19
ከሪትማም ተጕዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ።
- 20
ከሬሞን ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ።
- 21
ከልብናም ተጕዘው በሪሳ ሰፈሩ።
- 22
ከሪሳም ተጕዘው በቀሄላታ ሰፈሩ።
- 23
ከቀሄላታም ተጕዘው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ።
- 24
ከሻፍር ተራራም ተጕዘው በሐራዳ ሰፈሩ።
- 25
ከሐራዳም ተጕዘው በመቅሄሎት ሰፈሩ።
- 26
ከመቅሄሎትም ተጕዘው በታሐት ሰፈሩ።
- 27
ከታሐትም ተጕዘው በታራ ሰፈሩ።
- 28
ከታራም ተጕዘው በሚትቃ ሰፈሩ።
- 29
ከሚትቃም ተጕዘው በሐሽሞና ሰፈሩ።
- 30
ከሐሽሞናም ተጕዘው በሞሴሮት ሰፈሩ።
- 31
ከሞሴሮትም ተጕዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።
- 32
ከብኔያዕቃንም ተጕዘው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።
- 33
ከሖርሃጊድጋድም ተጕዘው በዮጥባታ ሰፈሩ።
- 34
ከዮጥባታም ተጕዘው በዔብሮና ሰፈሩ።
- 35
ከዔብሮናም ተጕዘው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።
- 36
ከዔጽዮንጋብርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት።
- 37
ከቃዴስም ተጕዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።
- 38
ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።
- 39
አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር።
- 40
በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ።
- 41
እነርሱም ከሖር ተራራ ተጕዘው በሴልሞና ሰፈሩ።
- 42
ከሴልሞናም ተጕዘው በፉኖን ሰፈሩ።
- 43
ከፉኖንም ተጕዘው በኦቦት ሰፈሩ።
- 44
ከኦቦትም ተጕዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ።
- 45
ከጋይም ተጕዘው በዲቦንጋድ ሰፈሩ።
- 46
ከዲቦንጋድም ተጕዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ።
- 47
ከዓልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ።
- 48
ከዓብሪምም ተራሮች ተጕዘው በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ባለው በሞዓብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ።
- 49
በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ።
- 50
እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው።
- 51
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ወደከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥
- 52
የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤
- 53
ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም።
- 54
ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።
- 55
የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።
- 56
እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።