Nehemiah 7
World English Bible (en) → Amharic Bible (am)
- 1
እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥
- 2
ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
- 3
እኔም። ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፤ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፥ ይቈልፉም፤ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቆችን አስቀምጡ አልኋቸው።
- 4
ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር።
- 5
አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።
- 6
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
- 7
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከነሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከሚስጴሬት፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና ጋር መጡ።
- 8
የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።
- 9
የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።
- 10
የኤራ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት።
- 11
ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት።
- 12
የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
- 13
የዛቱዕ ልጆች፥ ስምንት መቶ አርባ አምስት።
- 14
የዘካይ ልጆች፥ ሰባት መቶ ስድሳ።
- 15
የቢንዊ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት።
- 16
የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት።
- 17
የዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት።
- 18
የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት።
- 19
የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት።
- 20
የዓዲን ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ አምስት።
- 21
የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት።
- 22
የሐሱም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት።
- 23
የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ አራት።
- 24
የሐሪፍ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት።
- 25
የገባዖን ልጆች፥ ዘጠና አምስት።
- 26
የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች፥ መቶ ሰማንያ ስምንት።
- 27
የዓናቶች ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
- 28
የቤትዓዝሞት ሰዎች፥ አርባ ሁለት።
- 29
የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት።
- 30
የራማና የጌባ ሰዎች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ።
- 31
የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት።
- 32
የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሦስት።
- 33
የሁለተኛው ናባው ሰዎች፥ አምሳ ሁለት።
- 34
የሁለተኛው ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።
- 35
የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ።
- 36
የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት
- 37
የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አንድ።
- 38
የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።
- 39
ካህናቱ፤ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።
- 40
የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት።
- 41
የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።
- 42
የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት።
- 43
ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
- 44
መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ አርባ ስምንት።
- 45
በረኞቹ፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ መቶ ሠላሳ ስምንት።
- 46
ናታኒም፥ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥
- 47
የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥
- 48
የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥
- 49
የአጋባ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥
- 50
የራያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥
- 51
የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥
- 52
የቤሳይ ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥
- 53
የንፉሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥
- 54
የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥
- 55
የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥
- 56
የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
- 57
የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥
- 58
የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥
- 59
የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈከራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች።
- 60
ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
- 61
ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤
- 62
የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት።
- 63
ከካህናቱም የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች።
- 64
እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ።
- 65
ሐቴርሰታም። በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም አላቸው።
- 66
- 67
ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥
- 68
ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
- 69
ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ።
- 70
ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ።
- 71
የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ።
- 72
ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።