Lamentations 5
World English Bible (en) → Amharic Bible (am)
- 1
አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ።
- 2
ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።
- 3
ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል።
- 4
ውኃችንን በብር ጠጣን እንጨታችንን በዋጋ ገዛን።
- 5
አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፤ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።
- 6
ለግብጻውያንና ለአሦራውያን እንጀራ እንጠግብ ዘንድ እጅ ሰጠን።
- 7
አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን።
- 8
ባሪያዎች ሠልጥነውብናል፤ ከእጃቸው የሚታደገን የለም።
- 9
ከምድረ በዳ ሰይፍ የተነሣ በሕይወታችን እንጀራችንን እናመጣለን።
- 10
ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ።
- 11
በጽዮን ሴቶችን፥ በይሁዳም ከተሞች ደናግልን አጐሰቈሉ።
- 12
አለቆች በእጃቸው ተሰቀሉ፤ የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም።
- 13
ጕልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ።
- 14
ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጕልማሶች ከበገናቸው ተሻሩ።
- 15
የልባችን ደስታ ቀርቶአል፤ ዘፈናችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል።
- 16
አክሊል ከራሳችን ወድቆአል፤ ኃጢአት ሠርተናልና ወዮልን!
- 17
ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፤ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፤
- 18
ስለ ጽዮን ተራራ፥ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮችም ተመላልሰውባታልና።
- 19
አቤቱ፥ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
- 20
ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
- 21
አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።
- 22
ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል፤ እጅግ ተቈጥተኸናል።