Lamentations 3
World English Bible (en) → Amharic Bible (am)
- 1
አሌፍ። በቍጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።
- 2
ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ።
- 3
ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ።
- 4
ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ።
- 5
ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ።
- 6
ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ።
- 7
ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፤ ሰንሰለቴን አከበደ።
- 8
በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴን ከለከለ።
- 9
መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ።
- 10
ዳሌጥ። እንደሚሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ።
- 11
መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፤ ባድማ አደረገኝ።
- 12
ቀስቱን ገተረ ለፍላጻውም እንደ ጊጤ አደረገኝ።
- 13
ሄ። የሰገባውን ፍላጻዎች በኵላሊቴ ውስጥ ተከለ።
- 14
ለወገኔ ሁሉ ማላገጫ ቀኑንም ሁሉ መሳለቂያ ሆንሁ።
- 15
ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ።
- 16
ዋው። ጥርሴን በጭንጫ ሰበረ፥ በአመድም ከደነኝ።
- 17
ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፤ በጎ ነገርን ረሳሁ።
- 18
እኔም። ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ።
- 19
ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ።
- 20
ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች።
- 21
ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ።
- 22
ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።
- 23
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።
- 24
ነፍሴ። እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች።
- 25
ጤት። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።
- 26
ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
- 27
ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
- 28
ዮድ። እርሱ አሸክሞታልና ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ።
- 29
ተስፋ የሆነው እንደ ሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።
- 30
ጕንጩን ለሚመታው ይስጥ፥ ስድብንም ይጥገብ።
- 31
ካፍ። ጌታ ለዘላለም አይጥልምና፤
- 32
ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፤
- 33
የሰውን ልጆች ከልቡ አያስጨንቅም፥ አያሳዝንምም።
- 34
ላሜድ። በምድር የተጋዙትን ሁሉ ከእግሩ በታች ይረግጣቸው ዘንድ፥
- 35
የሰውን ፍርድ በልዑል ፊት ይመልስ ዘንድ፥
- 36
የሰውን ፍርድ ያጣምም ዘንድ ጌታ እሺ አይልም።
- 37
ሜም። ጌታ ያላዘዘውን የሚልና የሚፈጽም ማን ነው?
- 38
ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን?
- 39
ሕያው ሰው የሚያጕረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጕረመርም ስለ ምንድር ነው?
- 40
ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።
- 41
ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ።
- 42
በድለናል ዐምፀናልም፥ አንተም ይቅር አላልህም።
- 43
ሳምኬት። በቍጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፤ ገደልኸን፥ አልራራህም።
- 44
ጸሎት እንዳያልፍ ራስህን በደመና ከደንህ።
- 45
በአሕዛብ መካከል ጕድፍና ውዳቂ አደረግኸን።
- 46
ዔ። ጠላቶቻችን ሁሉ አፋቸውን ኣላቀቁብን።
- 47
ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን።
- 48
ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች።
- 49
- 50
ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዓይኔ ነፍሴን አሳዘነች።
- 51
ጻዴ። በከንቱ ነገር ጠላቶች የሆኑኝ እንደ ወፍ ማደንን አደኑኝ።
- 52
ሕይወቴን በጕድጓድ አጠፉ፥ በላዬም ድንጋይ ጣሉ።
- 53
በራሴ ላይ ውኆች ተከነበሉ፤ እኔም። ጠፋሁ ብዬ ነበር።
- 54
ቆፍ። አቤቱ፥ በጠለቀ ጕድጓድ ውስጥ ሆኜ ስምህን ጠራሁ።
- 55
ድምፄን ሰማህ፤ ጆሮህን ከልመናዬ አትመልስ።
- 56
በጠራሁህ ቀን ቀርበህ። አትፍራ አልህ።
- 57
ሬስ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ።
- 58
አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፥ ፍርዴን ፍረድልኝ።
- 59
በቀላቸውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ አየህ።
- 60
ሳን። አቤቱ፥ ስድባቸውንና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ፥
- 61
የተነሡብኝን ሰዎች ከንፈሮች ቀኑንም ሁሉ ያሰቡብኝን አሳባቸውን ሰማህ።
- 62
መቀመጣቸውንና መነሣታቸውን ተመልከት፤ እኔ መሳለቂያቸው ነኝ።
- 63
ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ትከፍላቸዋለህ።
- 64
የልብ ዕውርነትንና እርግማንህን ትሰጣቸዋለህ።
- 65
አቤቱ፥ በቍጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ።